Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home

ሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን

የሰሜን ጎንደር መስተዳደር ዞን በኢትዮጵያ የአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ጊዜ  በነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ከአሁኑ ደቡብ ጎንደር መስተዳድር ዞን ጋር በአንድነት ተጠቃሎ በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት በመባል ይጠራ በነበረው  የተጠቃለለ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ንጉሳዊው የመንግስት መዋቅር በየካቲት ወር 1966 ዓ.ም ጀምሮ በአብዮታዊ መንግስት ከተቀየረ በኋላ በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት የሚለው መጠሪያ  የጎንደር ክፍለ ሃገር ተብሎ  ሲጠራ ከቆየ በኋላ በኢትዮጵያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አካባቢ ተብሎ ሲጠራ ቆይቷል ፡፡ ከዚያም የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር አካባቢ እየተባለ መጠራቱ እስከ ከደርግ መውደቅ ቀጥሎ ከግንቦት 1983 ዓ.ም  በኋላ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት በክልል ሶስት መስተዳድር የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን በሚል መጠሪያ ከቆየ በኋላ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን ተብሎ እንደነበር በዞኑ አስተዳደር ካለው ነባር መዝገብ ቤት ካሉ ገዥዎች አስተዳዳሪዎች ይጻጻፉባቸው የነበሩ ደብዳቤዎችና ሌሎች መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ዋና ከተማን በተመለከተ በእንደራሴዎችናገዢዎች በአስተዳዳሪዎች ጊዜ አንስቶ የመሪዎች መቀመጫ  ጎንደር ከተማ ናት፡፡በጌምደርና ስሜን ጠቅላይ ግዛትና ጎንደር ክፍለ ሀገር በሚባል መጠሪያ ጊዜ የነበረው የአስተዳደር እርከን

1. ስሜን  አውራጃ

2. ወገራ አውራጃ

3. ጎንደር ዙሪያ አውራጃ

4. ጭልጋ አውራጃ

5. ሊቦ አውራጃ

6. ደብረታቦር አውራጃ

7. ጋይንት አውራጃ ነበሩ፡፡

ሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከሚገኙ 10 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ አንዱና ከክልሉ በቆዳ ስፋትም ሆነ በህዝብ ብዛት ቀዳሚ ነው፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ የሆነችው ታሪካዊቷ ጎንደር የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ ከተማ ከሆነችው ባህርዳር በሰሜን አቅጣጫ 175 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

የዞኑ አወቃቀር በ20 የገጠር ወረዳዎችና በ5 የከተማ አስተዳደሮች በ1 ሜትሮፐሊታንት ከተማ/ጎንደር ከተማ/ በ519 የገጠርና 59 የከተማ  ቀበሌዎችን  በአጠቃላይ 578 ቀበሌዎችን የያዘ ነው፡፡ ምንጭየዞኑ ገ/ኢ/ል/መምሪያ 2006 እትም መጽሄት

የዞኑ አዋሳኞች በሰሜን ትግራይ ክልል፣ በደቡብ ከደቡብ ጎንደርና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣ በምዕራብ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልና ሱዳን ፣ በስተምስራቅ ከደቡብ ጎንደርና ከዋግ ህምራ ዞኖች  ጋር ይዋሰናል፡፡

የመሬት አቀማመጥ

የዞኑ የመሬት አቀማመጥ ከባህር ጠለል በላይ 1500 እስከ 4620 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን ተራራማ፣ኮረብታማ፣ሜዳማና ገደላማ የመሬት አቀማመጥ አለው፡፡

ከክልሉ ግብርና ቢሮ በተገኘ መረጃ መሰረት የዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 48,621.21 ካሬ ኪ/ሜ ሲሆን

የተዳፋትነት ሁኔታ፡

- 0-10%          25.93%

- 10-25           19.59%

- 25-35%         14.97%

- 35-50 %         12.47%

>50%                27.04% ነው

የመሬት የሰብል አብቃይነት

- - ለዓመታዊ ሰብሎች 900,207 ሄክታር፣

- ቋሚ ተክሎች4,390 ሄክታር፣

- መስኖ 6,700ሄክታር፣

- ደንና ቁጥቋጦ735,432 ሄክታር፣

- ግጦሽ 770,340 ህክታርና

- ውኃ አዘል መሬት 306,048 ሄክታር ነው፡፡

የአየር ቀጠና ክፍፍልን በተመለከተ

- ውርጭ 1.2%

- ደጋ 17.8%

- ወይና ደጋ 44%

- ቆላ 37%

የዝናብና  የሙቀት መጠን

- ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከፍተኛ 1700ሚ/ሜ

- ዝቅተኛ 1172ሚ/ሜ ነው፡፡

- የዓመቱ ከፍተኛ ሙቀት 42oc ሲሆን  ዝቅተኛው 10oc ነው፡፡

የሰብል ምርት

- 60,400 ሄክታር  ያክል በሚገመት የመሬት ሽፋን ላይ ዕጣንና ሙጫ ዛፍ ሃብት ይገኝበታል፡፡ አማካኝ የመሬት ይዞታ በቤተሰብ 1.5 ሄክተር ያክል  ሲሆን ከመሬቱ የሰብል ሽፋን አንጻር

- የብዕር ሰብሎች 30%

- የአገዳ ሰብሎች 32%

- የጥራጥሬ ሰብሎች 9%

- የቅባት እህሎች 24%

- ሌሎች ሰብሎች 5% ነው፡፡

የዞኑ ምዕራባዊና የጣና ተፋሰስ ወረዳዎች በቂ ዕርጥበት የሚያገኙና ለምግብነት የሚውሉና ኤክስፖርት የሚደረጉ የግብርና ምርቶችን በማምረት ከመታወቃቸውም በላይ የክልሉ አረንጓዴ ቀበቶ የሚባለው  የአላጢሽ ብሄራዊ ፓርክም ከዞኑ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ  ወረዳ ቋራ ውስጥ ይገኛል፡፡

የዞኑ ሰሜናዊና የሰሜን ምስራቅ ወረዳዎች በዝናብ አጠርነት የሚመደቡ ቢሆኑም የሰሜናዊ ወረዳዎች ደጋማው ክፍል የቢራ ብቅል ገብስ ለማምረት እጅግ ተስማሚ ናቸው፡፡ የሰሜን ምስራቁ ክፍል  ካለው የመሬት አቀማመጥ አመቺነት  የተለያዩ የርጥበት ዕቀባ ተግባራትን በማከናወን ሰፊ የሆነ የጤፍ፣ማሸላና ሽምብራ ሰብሎችን ማማረት ያስችላል፡፡

ዞኑ በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ትምህርትና ባህል ድርጅት (UNESCO) የተመዘገቡ የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ መገኛ ነው፡፡ ሰንሰለታማ ተራሮችና የምስራቅ አፍሪቃ ከፍተኛው አምባ ምድር ራስደጀን፣የዋሊያ፣የጭላዳ ዝንጀሮ፣ቅልጥም ሰባሪ ሞራ፣ ቀይ ቀበሮ መገኛ ነው፡፡

የህዝብ ብዛት

የህዝብ ብዛት በተመለከተ 1997 ዓ.ም የህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት አጠቃላይ ነዋሪን በተመለከተ 1,744,757 ወንድና 1,721,468 ሴት በድምሩ 3,466,225 ህዝብ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ ውስጥ  በገጠር የሚኖረው 2905764(83.83%)ነው፡፡ 43,2986 ኣባወራና 83,461 እማወራ በድምሩ 516,757 የገጠር ቤተሰብ ኃላፊዎችን የያዘ ሲሆን የህዝብ ጥግግቱ 77 ህዝብ በካሬ ኪሎሜትር ነው፡፡

ከሰው ኃብቱና ከመሬት ሀብቱ በተጨማሪ ሃብትን ለማፍራት የሚያስችሉ ገጸ ምድር ውኃዎች ሽንፋ፣አይማ፣ ጓንግ፣አንገረብ፣መገጭ፣መና፣ሆጣ ድማዛ ወዘተ የሚገኙበት ሲሆን ከኢትዮያ ትልቁ ሃይቅ ጣና ከ50% በላይ አካሉ የሚገኘው በዚሁ ዞን ውስጥ ነው፡፡

Last Updated (Monday, 09 January 2017 11:09)

 
ፈልግ
ስለ ድረ ገጹ ያለዎት አስተያየት ምንድነው?
 
Latest News

የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ድረ ገጹን አስተዋወቀ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

የሰሜን ጎንደር ኢኮቴ የሥራ ሂደት በ24 ወረዳዎች ለሚገኙ ሙያተኞቹ በድረ ገጽ ልማት ዙሪያ ለ10 ቀናት ያህልስልጠና ሰጠ

ተጨማሪ

© 2006 Copy Right All Rights Reserved
Developed By North Gondar Zone Admin Office;Information Communication Technology Core Process